News News

80 ኪሎሜትር የሚረዝመው የቱሉ ቦሎ - ኬላ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ወደ አሰፓልት ንጥፍ ስራ ተሸጋገረ ።

80 ኪሎሜትር የሚረዝመው የቱሉ ቦሎ  - ኬላ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት  ወደ አሰፓልት ንጥፍ ስራ ተሸጋገረ ።
 
እስካሁን ባለው አፈጻጸም 26 ኪሎሜትሩ ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪ የፕሮጀክቱን ክፍሎች አስፓልት ለማልበስ እየተሰራ ነው። በአሁኑ ወቅት የአፈር ቆረጣ ና የአፈር ሙሌት ፤ የቤዝ ኮርስ ስራ ፤ የአስፋልት እና  ፤ የድልድይ ስራዎች በትኩረት እየተሰሩ ነው። በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው የቱሉ ቦሎ - ኬላ የመንገድ ፕሮጀክት የኦሮሚያ ክልልን ከአጎራባች የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ጋር የሚያገናኝ ወሳኝ ፐሮጀክት ነው፡፡ ከቡታጂራ አዲስ አበባ ከሚወስደው አውራ መንገድ ጋርም በአቋራጭ ያስተሳስራል ፡፡ የቱሉ ቦሎ - ኬላ የመንገድ ፕሮጀክት እየተገነባ የሚገኘው ከመንግስት በተመደበ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር  በጀት ነው፡፡ ግንባታውን የሚያካሂደው ሁናን ሁንዳ ሮድ ኤንድ ብሪጅ የተሰኘ ዓለም ዓቀፍ የስራ ተቋራጭ ድርጅት ሲሆን  የመንገዱን ጥራት በመቆጣጠርና በማማከር አየሰራ ያለው ደግሞ የተባበሩት የምህንድስና አማካሪዎች ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ነው፡፡ 3 ወረዳዎችን አቋርጦ ኬላ ከተማ የሚደርሰው ይህ መንገድ በአካባቢው በሚገኙ በገብስ ፤ ስንዴ ፤ ባቄላና አተር ምርቶቹ የታወቀ በመሆኑ ምርቶቹን በፍጥነት ወደ ማእከላዊ ገበያ እንዲደርስ ስለሚያስችል ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ያጎለብታል፡፡ የቱሉ ቦሎ - ኬላ የመንገድ ፕሮጀክት በቀጣይ አመት ለማጠናቀቅ ታቅዶ በትኩረት እየተሰራ ነው።