News News

የጊንጪ ሽኩቴ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የግንባታ እንቅስቃሴ

የጊንጪ ሽኩቴ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የግንባታ እንቅስቃሴ በትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታው  አቶ ካሳሁን ጎፌ እና በኢመባ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኘ እንዲሁም በተቋሙ የስራ ሃላፊዎች  በመስክ የስራ ቅኘት ተጎብኝቷል።
59ኪ.ሜትር ርዝመት የሚሸፍነውን ይህንኑ ፕሮጀክት ነው የተቃኘው።የመንገድ ፕሮጀክቱ ቀደም ብሎ በወሰን ማስከበር እና ተያያዥ ችግሮች ሳቢያ በእቅዱ መሰረት ለመስራት ሲቸገር ቆይቶ በአሁኑ ወቀት ያሉት ዋና ዋና ችግሮች በመቀረፍቸው ፕሮጀክቱ በጥሩ ሁኔታ በመከናወን ላይ መሆኑ ተገምግሞል ።በዚህም በአሁኑ ወቅት  የአስፖልት ማንጠፍ  ስራ የተጀመረ ሲሆን በያዝነው አመት መጨረሻ ድረስም  ዋና ዋና ስራዎች እንደሚጠናቀቁ ይጠበቃል።ይህ እንዲሆን አሁንም ከወሰን ማሰከበር ጋር ተያይዞ ያልተፈቱ ችግሮችን ለማቃለል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ይበልጥ ተቀራርቦ እንዲሰራም  የስራ ሃላፊዎቹ አሳስበዋል።
የዛሬው የመስክ ቅኘት አላማም የፖሮጀክቱን ሂደት በአካል   ከመመልከት ባለፈ  የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የበኩሉን ሚና ለማበርከት ያለመ ነው። የጊንጪ ሽኩቴ  መንገድ ከዚህ ቀደም በጠጠር ደረጃ የነበረ ሲሆን ካለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ አንጻር በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እየተገነባ ነው ጨረታውን አሸንፎ ግንባታውን በማከናወን ላይ የሚገኘው የተቋራጩ ባለቤት አቶ ገምሹ በየነ ያሉ ችግሮችን በጋራ በመፍታት ፕሮጀክቱን በጥራት አጠናቆ ለማስረከብ ይበልጥ እየሰራን ነው ብለዋል።ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ለመስመሩ ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ  እና ማህበራዊ ፍይዳዎችን የሚያጎናጽፍ ነው።በተያያዘ ዜናም የስራ ሃላፊዎቹ በዛሬው የመስክ ቅኝታቸው ከ1ነጥብ 26ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በመገንባት ላይ የሚገኘውን የሽኩቴ ጩሉጤን 63ነጥብ 2ኬሜ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን ቃኝተዋል።ከመልካ ምድራዊ አቀማመጥ ጋር ተያይዞ የአፈር መንሸራተትና ናዳ የሚስተዋልባቸውን ስፍራዎችን ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠትም ይበልጥ ይሰራል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎቹ  ከወሰን ማስከበር እና ከግብአት አቅርቦት ጋር የተያያዙ ችግሮች እንዲፈቱ አቅጣጫንም አሰቀምጠዋል ።ለፕሮጀክቱ ተግዳሮት የሚሆኑ ችግሮችን በቀጣይ በጋራ በመፍታት ስራው እንዲፋጠን ይበልጥ  የጎላ ሚና እንደሚያበረክቱም የስራ ሃላፊዎቹ አረጋግጠዋል።መንገዱ ካለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፍይዳ አኳያ ኮንትራክተሩም ሆነ አማካሪ ድርጅቱ በትኩረት እንዲሰሩም አስገንዝበዋል::