News News

የዳዬ- ጭሪ- ናንሴቦ74 ኪ.ሜየመንገድፕሮጀክትበአስፋልትኮንክሪትደረጃእየተገነባነው።

የዳዬ - ጭሪ - ናንሴቦ 74 ኪ .ሜ የመንገድ ፕሮጀክት  በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እየተገነባ ነው ።

ፕሮጀከቱ በአሁናዊ አፈጻጻሙ 17 ኪ.ሜ  የሚሸፍን የአስፋልት ኮንክሪት ንጣፍ ስራንም አከናውኗል፡፡ የፕሮጀክቱ ቀሪ  ክፍሎችንም በአሰፖልት ለማልበስ በትኩረት እየተሰራ ነው። ፕሮጀክቱ አሁን ላይ እስከ 30 ሜትር ከፍታ ያላቸው 3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሜትር ኩብ የሚሆን የአፈር ቆረጣ ስራዎች እና  የአፈር ጠረጋ እና  ድልዳሎ  እንዲሁም የድልድይ እና የውሀ ማፍሰሻ ቦዮችን የመገንባት ስራ በተመሳሳይ  እየተከናወነ ነው፡፡ የሲዳማ እና የኦሮሚያ ክልሎችን በአቋራጭ  የሚያስተሳስረው ይህ የመንገድ ፕሮጀክት በቀጣይ ቀሪ የመንገዱን ክፍሎች አስፋልት የማልበስ ስራዎችን  ለማካሄድ ይረዳ ዘንድ ከወዲሁ  የመሬት ዝግጅት እና የጠጠር መፍጨት  ስራዎች ተመቻችተዋል  ። የዳዬ - ጭሪ - ናንሴቦ  የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ  እየተገነባ የሚገኘው ከመንግስት በተመደበ  1 ነጥብ 68 ቢሊዮን ብር በጀት ነው። ግንባታውን የሚያካሂደው ቻይና ውይ ሊሚትድ የተባለ አለም አቀፍ  የስራ ተቋራጭ  ድርጅት  ሲሆን  የመንገዱን ጥራት በመቆጣጠር እና በማማከር የሚሳተፈው  ሲቪል ወርክስ ኮንሰልትግ እንጂነርስ የተባለ አገር በቀል አማካሪ ድርጅት ነው፡፡ መንገዱ በአስፋልት ኮንክሪት ተገንብቶ ሲጠናቀቅ በቀጣይ በሀዋሳ አድርጎ  ወደ ሞያሌ የሚሄደውን ዋና  መንገድ ከሻሸመኔ ወደ ባሌ ጎባ ከሚወስደው ሌላ ዋና አውራ መንገድ ጋር በአቋራጭ ያስተሳስራል፡፡ ከዛም ባለፈ አካባቢው በከፍተኛ ደረጃ በቡና እና በፍራፍሬ ምርቱ የታወቀ በመሆኑ ምርቶቹን በፍጥነት ወደ ማእከላዊ ገበያ እንዲቀርብ ስለሚያስችል ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ያጎለብታል በአሁን ሰአት 73 ኪሎ ሜትሩን የጠጠር መንገድ  በተሸከርካሪ  ለመጓዝ  ከግማሽ ቀናት በላይ ሲወስድ በክረምት ወቅት ደግሞ ግልጋሎት የሚሰጥ አልነበረም፡፡  የመንገድ ፕሮጀክቱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ  በአንድ ሰአት ተኩል ጊዜ ውስጥ  መጓዝ ስለሚያስችችል  በከፍተኛ ደረጃ የትራንስፖርት ጊዜን እና ወጪን ይቀንሳል።
በመንገዱ አስቸጋሪነት ሳቢያ  መስመሩ ላይ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ባለመኖራቸው ነዋሪው የትራንስፖርት ግልጋሎት በአማራጭነት ይጠቀም የነበረው በሞተር ሳይክል ፣ በበቅሎ አልያም በእግር መጓዝ  የነበረውን  በቀጣይ  በመፍታት በቂ የትራንስፖርት አማራጮችን ያስፋፋል፤የዳዬ - ጭሪ - ናንሴቦ  መንገድ ስራ   የሚገኝበት አካባቢ ዝናባማ በመሆኑ በአመት ውስጥ አራት ደረቅ ወራትን ብቻ ነው ተቋራጩ ለመንገድ  ግንባታ እየተጠቀመ ያለው በተጨማሪም መልክአ ምድራዊ አቀማመጡ ውሃ አዘል መሬት  መሆኑ   ተደጋጋሚ የመሬት መንሸራተት እና ናዳ ማስከተሉ የፕሮጀክቱ ተግዳሮቶች ናቸው። ይህን ተግዳሮት ከመቅረፍ አንጻር የግንባታ ስራ ተቋራጩ ባለው ደረቃማ ወቅት ቀሪ ስራዎችን በአፋጣኝ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ጊዜን በመመደብ ምሽትን ጨምሮ ግንባታ እያካሄደ ይገኛል።