News News

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የጊምባ-ተንታ-ተንታ-መገንጠያ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታስራን በይፋ አስጀመሩ።

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን  የጊምባ-ተንታ-ተንታ-መገንጠያ  የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታስራን በይፋ አስጀመሩ።

በተንታ ወረዳ በአጅባር ከተማ  በተካሄደው የፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ፣ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ብናልፍ አንዱአለም ፣የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራልና እና የክልል የስራ ሃላፊዎች ታድመዋል።መንግስት በመደበው ከ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው የጊምባ -ተንታ-ተንታ መገንጠያ 80.2 ኪ. ሜ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የህዝቡን የአመታት ጥያቄ ምላሽ የሰጠ ነው ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ።ለረዥም ዓመታት የመንገድ መሰረተ ልማት ባለመኖሩ የዚህ አካባቢ ነዋሪ በከፍተኛ ሁኔታ ሲቸገር እንደቆየም ተናግረዋል። ይህ ታሪክ ሊሆን በመቃረቡ  ለመላው ህዝብ   የእንኳን ደስ ያላችሁመልክታቸውንአስተላልፈዋል። ምክትል ጠቅላይ  ሚኒስትሩ አካባቢውን ፣ ከክልሉ፣ ክልሎችን ከሀገሪቱ የወጪ ገቢ ንግድ ጋር የሚያስተሳስሩ ሌሎች በርካታ ፕሮጀክቶችን ደረጃ በደረጃ እንዲተገበሩ መንግስት አቅጣጫ ማስቀመጡንም አብራርተዋል።

ይህ ፕሮጀክትም ከተያዘለት ጊዜ በፊት  እንዲጠናቀቅ  የአካባቢው ነዋሪዎች እና የአመራር አካላት በብርታትና በጥንካሬ ከተቋራጮቹ  ጋር  በመሆን የሚያጋጥሙ የወሰን ማስከበር ችግሮችን ቀድመው እንዲፈቱም አሳስበዋል። የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ በበኩላቸው ፕሮጀክቱን በስኬት ለማጠናቀቅ ተገቢውን የድጋፍ፣ የክትትል እና የቁጥጥር ሥርዓትን  እንደሚያደርግ  ገልፀዋል።መላው የአካባቢው ነዋሪ ፣የሥራ ተቋራጩም ሆነ የአማካሪ ድርጅቱ የተጣለባቸውን ከፍተኛ ሀላፊነት በብቃት እንዲወጡም  አስገንዝበዋል ።እንዲሁም ግንባታውን የሚያከናውነው የስራ ተቋራጭ የድርጅቱ  ተወካይ በገቡት የኮንትራት ውሉ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ፕሮጀክቱን ገንብቶ ለማስረክብ  ቃል ገብተዋል።አጠቃላይ ስለ ፕሮጀክቱ ዝርዝር መረጃ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ ይገኛል።የጊምባ-ተንታ-ተንታ መገንጠያ የመንገድ ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ 568 ኪ. ሜትር  ይርቃል።የፕሮጀክቱ ስም ፦ ጊምባ-ተንታ-ተንታ መገንጠያ ርዝመት ፦     80.2 ኪ. ሜትር የሥራ ተቋራጭ፡- ጂያንግዢ ዘ ሰከንድ ኮንስትራክሽን የቻይና ስራ ተቋራጭ ነው።የግንባታው አይነት ፡-DBB አማካሪ ድርጅት፡- ሲቪል ወርክስ ኢንጂነርስ፣የኮሪያ ካምፓኒ ዮሺን ኮርፖሬሽን እንዲሁም ጂ እና ዋይ በጋራ በመተባበር  የግንባታ ወጪ፡- 2,185,228,256.12 የግንባታው ወጪ ሽፋን፡-   የኢትዮጵያ መንግስት የግንባታው ደረጃ ፦ አስፋልት ኮንክሪት ለግንባታው የተሰጠው ጊዜ፡- 3 ዓመት

መንገዱ የሚያቋርጥባቸው ወረዳዎች ፦ ለጋምቦ፣ተንታ፣ደላንታ በርካታ ቀበሌዎች በመንገድ ፕሮጀክቱ ውስጥ የሚካተቱ ስራዎች የአፈር ቆረጣና ሙሌት ሥራ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ሥራ የሁለት ድልድዮች ስራ ትንንሽና መካከለኛ የተፋሰስ ስራዎች የመንገድ ዳር ትራፊክ ምልክቶች ግንባታ ሥራ እንዲሁም በርካታ የስትራክቸር ሥራዎች የመንገድ ፕሮጀክቱ መገንባት ሁለንተናዊ ፋይዳ በጠጠር ደረጃ የነበረው የመንገዱ ግንባታ ተገንብቶ በሚጠናቀቅበት ወቅት ከዚህ በፊት በአካባቢው የነበረውን የትራንስፖርት ችግር በመቅረፍ  ህብረተሰቡ ተሸከርካራዎችን ተጠቅሞ በተመጣጣኝ ዋጋ ወደፈለገው ቦታ የሚንቀሳቀስበትን ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ከዚህ ቀደም ከደሴ ተነስቶ ተንታ ለመድረስ በመንገዱ መበላሸት ሳቢያ ይደርስ የነበረውን የዙሪያ ጥምጥም መንገድ በአንድ ሰዓት ተኩል ይቀንሰዋል።የመንገድ ፕሮጀክቱ መገንባት ግንባታው ከሚካሄድበት አስራ አምስት ኪ. ሜትር ወደ ጎን ተገንጥሎ መቅደላ የሚገኘውን የሀጼ ቴዎድሮስ ታሪካዊ ሰፍራ የጀግንነት ስፍራ እንዲሁም ለነጻነት ትግል ሲጠቀሙበት የነበረውን ሴባስቴፖል መድፍ ለመጎብኘት ለቱሪስት ምቹ ሁኔታን ከመፍጠርም አልፎ የቱሪዝም ፍሰቱን በመጨመር የውጭ ምንዛሬን ከማምጣት አኳያ ሃገራዊ ፋይዳው የጎላ ነው።የአካባቢው ነዋሪዎች  የሰብል ምርቶችን እንደ ጤፍ፣ገብስ፣ባቄላ እንዲሁም የቁም እንስሳት ውጤቶች ትራንስፖርትን ተጠቅመው  ወደ ገበያ አውጥቶ በመሸጥ ነዋሪው  ከምርታቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡በመስመሩ የሚገኙ ዞኖች ወረዳዎች እና ቀበሌዎች በአስፋልት መንገድ በቅርበት ያስተሳስራል።