Invitation for Bid




















Top News
80 ኪሎሜትር የሚረዝመው የቱሉ ቦሎ - ኬላ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ወደ አሰፓልት ንጥፍ ስራ ተሸጋገረ ።
እስካሁን ባለው አፈጻጸም 26 ኪሎሜትሩ ሙሉ ለሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀሪ የፕሮጀክቱን ክፍሎች አስፓልት ለማልበስ እየተሰራ ነው። በአሁኑ ወቅት የአፈር ቆረጣ ና የአፈር ሙሌት ፤ የቤዝ ኮርስ ስራ ፤ የአስፋልት እና ፤ የድልድይ ስራዎች በትኩረት እየተሰሩ ነው። በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው የቱሉ ቦሎ - ኬላ የመንገድ ፕሮጀክት የኦሮሚያ ክልልን ከአጎራባች የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ጋር የሚያገናኝ ወሳኝ ፐሮጀክት ነው፡፡ ከቡታጂራ አዲስ አበባ ከሚወስደው አውራ መንገድ ጋርም በአቋራጭ ያስተሳስራል ፡፡ የቱሉ ቦሎ - ኬላ የመንገድ ፕሮጀክት እየተገነባ የሚገኘው Read More
ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰትን በማስተናገድና በአገልግሎት ብዛት ለጉዳት የተዳረገው የጊቤ ወንዝ - ጅማ መንገድ ከባድ ጥገና እየተደረገለት ነው።
167 ኪ.ሜትር የሚረዝመው የጊቤ ወንዝ - ጅማ መንገድ በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በጅማ ዲስትሪክት ነው የከባድ ጥገና ስራውን ማከናወን የጀመረው። የዲስትሪክቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ደመቀ የጊቤ ወንዝ - ጅማ መንገድ ከሚሰጠው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ አኳያ ከባድ ጥገና ማድረጉ ወሳኘ በመሆኑ ስራው መጀመሩን ተናግረዋል። በአሁን ወቅትም ከስልሳ ሚልዮን ብር በላይ በጀት ተይዞለት በራስ ሀይል የከባድ ጥገና ስራው በጥሩ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል። አጠቃላይ ጥገናው የጥራት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የአገልግሎት ጊዜው ዘላቂ እንዲሆን Read More
የጋሸና-ላሊበላ-ሰቆጣ መንገድ አካል የሆነው የጋሸና-ቢልባላ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ከአጠቃላይ 105 ኪ.ሜ ርዝመት ውስጥ 87 በመቶ የደረሰ ሲሆን በተያዘው ዓመት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል። የጋሸና-ቢልባላ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ በአሁኑ ወቅት 78 ኪ.ሜትሩ የአስፋልት ንጣፍ ስራው ተከናውኗል።ፕሮጀክቱን 1.87 ቢሊዮን ብር በሆነ ወጪ በመገንባት ላይ የሚገኘው አለማቀፉ ቻይና ሬል ዌይ ኢንጅነሪንግ ቁጥር 3 የስራ ተቋራጭ ነው። የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ኢንጂነር ዘውዴ እና ዋይ ኤል ኤስ ኢንጂነሪንግ አማካሪ ድርጅቶች በጣምራ እያከናወኑት Read More
ኢትዮጵያን ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚያስተሳስረው የዲማ - ራድ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ።
6060 ነጥብ 2 ኪ .ሜ እርዝመት ያለው ይኸው የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፍጻሚውን ማገኘቱ አማራጭ የገቢ ወጪ ንግድን ለማሳለጥ ከፍተኛ ጠቀሜታን ያበረክታል።የክልሉን የመንገድ ትራንስፖርት ትስስርን ከማቀላጠፉም በላይ ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር ያላትን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የማህበራዊ እና የኢኮኖሚ እንዲሁም የንግድ ልውውጥን የተሳለጠ ከማድረግ አኳያ የመንገዱ ፋይዳ ከፍተኛ ነው፡፡የዲማ - ራድ ድልድይ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ለሀገራችን ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝላትን ቡናን ጨምሮ የፍራፍሬ ፣ ማር እና ቅመማ ቅመም ምርት Read More
የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የጊምባ-ተንታ-ተንታ-መገንጠያ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታስራን በይፋ አስጀመሩ።
በተንታ ወረዳ በአጅባር ከተማ በተካሄደው የፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ፣ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ብናልፍ አንዱአለም ፣የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራልና እና የክልል የስራ ሃላፊዎች ታድመዋል።መንግስት በመደበው ከ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው የጊምባ -ተንታ-ተንታ መገንጠያ 80.2 ኪ. ሜ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የህዝቡን የአመታት ጥያቄ ምላሽ የሰጠ ነው ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ።ለረዥም ዓመታት Read More
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሀይቅ-ቢስቲማ-ጭፍራ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታስራን ዛሬ በይፋ አስጀመሩ።
በወረባቦ ወረዳ በቢስቲማ ከተማ ላይ በተካሄደው የፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ብናልፍ አንዱአለም ።፣የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራልና እና የክልል የስራ ሃላፊዎች ታድመዋል። መንግስት በመደበው ከ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው የሀይቅ- ቢስቲማ -ጭፍራ 74.3 ኪ. ሜ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የህዝቡን የአመታት ጥያቄ Read More
በባህርዳር ከተማ እየተገነባ የሚገኘው አዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ የግንባታ ስራ እየተፋጠነ ይገኛል፡፡
የፕሮጀክቱን የስራ እንቅስቃሴ እና የባህርዳር ጢስ እሳት የመንገድ ግንባታ ስራን በዛሬው እለት በትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታው አቶ ካሳሁን ጎፌ ፣በኢመባ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኘ እና የተቋሙ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በመስክ የስራ ቅኘት ተጎብኝቷል።አዲሱ የአባይ ወንዝ ድልድይ 380 ሜትር ርዝመት እና 43 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ድልድይ ነው።በጉብኝቱ ወቅት ፕሮጀክቱ ላይ በዋነኛነት የድልድይ ተሸካሚ ምሰሶዎችን (piers) ለአርማታ ሙሌት ስራ ማመቻቸት እንዲሁም የድጋፍ ግንቡን ከመሬት በታች የድልድዩ የቋሚ ተሸካሚ መሰረቶች (Abutment piles) Read More
59ኪ.ሜትር ርዝመት የሚሸፍነውን ይህንኑ ፕሮጀክት ነው ዛሬ የተቃኘው።የመንገድ ፕሮጀክቱ ቀደም ብሎ በወሰን ማስከበር እና ተያያዥ ችግሮች ሳቢያ በእቅዱ መሰረት ለመስራት ሲቸገር ቆይቶ በአሁኑ ወቀት ያሉት ዋና ዋና ችግሮች በመቀረፍቸው ፕሮጀክቱ በጥሩ ሁኔታ በመከናወን ላይ መሆኑ ተገምግሞል ።በዚህም በአሁኑ ወቅት የአስፖልት ማንጠፍ ስራ የተጀመረ ሲሆን በያዝነው አመት መጨረሻ ድረስም ዋና ዋና ስራዎች እንደሚጠናቀቁ ይጠበቃል።ይህእንዲሆንአሁንምከወሰንማሰከበር ጋር ተያይዞ ያልተፈቱ ችግሮችን ለማቃለል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ይበልጥ ተቀራርቦ እንዲሰራም Read More
የሀዋሳ - ጩኮ 66 ኪ.ሜ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ ።
የሞምባሳ - ናይሮቢ - አዲስ አበባ የመንገድ ኮሪደር አካል የሆነው የሀዋሳ - ጩኮ 66 ኪ.ሜ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ስራ ተጠናቀቀ።አጠቃላይ የፕሮጀክቱን የማጠቃለያ ስራን የተመለከተ የመስክ የስራ ስምሪት በስፍራው ተካሂዷል ።በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ የተገነባው የሀዋሳ - ጩኮ መንገድ በመስመሩ ላይ የሚገኙትን ከተሞች ፣ የእርሻና የኢንዱስትሪ ዞኖች እንዲሁም የቱሪስት መስህብ የሆኑ ስፍራዎችን ዘመናዊ በሆነ መንገድ በማስተሳሰር የጉዞ ጊዜንና ወጪን በመቀነስ ረገድ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡በደቡብ የኢትዮጵያ የሀገራችን ክፍል የሚመረቱ የግብርና እና የኢንደስትሪ Read More
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ በኢ.መ.ባ. ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የማነቃቂያ ዘመቻ እየተካሄደ ነው ፡፡
እየተካሄደ ባለው በዚሁ የቅስቀሳ ዘመቻ ላይም ለባለስልጣኑ መ/ቤት ሰራተኞች የተለያዩ ወረርሽኙን የተመለከቱ ግንዛቤ ሰጪ ትምህርቶች እየተሰጣቸው ይገኛል።ከዚህም ባለፈ በተቋሙም ባሉ እና የተለያዩ የሰዎች ምልልስ በሚዘወተርባቸው ስፍራዎች የኬሚካል ርጭት ተካሂዷል፡፡ እንዲሁም ለሰራተኛው የሙቀት መጠን መለካት ተግባራት መከናወናቸውን ቀጥለዋል ።ለባለሥልጣኑ ሰራተኞች እና ባለጉዳዮች ወረርሽኙን የተመለከቱ የተለያዩ መልእክቶችን ያዘሉ በራሪ ወረቀቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች እደላም እንዲሁ በመካሄድ ላይ ይገኛል ። Read More
ከዲቾቶ ተነስቶ በልሆ የሚዘልቀው መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ፡፡
የዲቾቶ - ጋላፊ መገንጠያ /ዶቢ- ኤሊዳር - በልሆ የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ ፡፡አዲሱን የታጁራ ወደብ ለመጠቀም የሚያስችለው ፕሮጀክቱ በአፋር ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን 78 ኪ.ሜ ርዝመት አለው ፡፡የመንገዱ ግንባታ ያካሄደው መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተባለ የመንግስት ልማት ድርጅት ነው ፡፡ ኢንጂነር ዘውዴ እስክንድርና ከሲም አማካሪ መሃንዲስ በጋራ ፕሮጀክቱን በአማካሪነት እና በተቆጣጣሪነት ተሳትፈዋል፡፡መንገዱን ለመገንባት 2.4 ቢሊዮን ብር ወጪን ጠይቋል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት መንገዱን ለመገንባት የዋለውን ReadMore
ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን 2 ሚልየን ችግኞችን ለመትከል የያዘውን እቅድ እውን ለማድረግ መርሃ ግብሩን ጀምሯል።
በጉለሌ የዕጽዋት ፓርክ በተካሄደው የችግኝ ተከላ የማስጀመር መርሃ ግብር ላይ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ፣ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ታደመዋል። በዚህም ከ500 በላይ አገር በቀል ችግኞችን የስራ ሃላፊዎቹ በስፍራው ተክለዋል በፕሮግራሙ ላይ የኢመባ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሀብታሙ ተገኘ በሃገር አቀፍ ደረጃ የአረንጓዴ አሻራን ለማሳረፍ የተያዘውን ሀገራዊ ሃላፊነት ለመወጣት የሁለት ሚሊየን የችግኝ ተከላ ፕሮጀክት በመቅረጽ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።በተጨማሪም ከዋናው መስሪያቤት የማኔጅመንት አባላት Read More